መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 11፤2015-የኢኳዶር ፕሬዝዳንታዊ እጩዋ ለ24 ሰዓታት በሙሉ ጥይት የሚከላከል ልብስ እየለበሰች መሆኑ ተነገረ

አንድሪያ ጎንዛሌዝ በየቀኑ 24 ሰአታት ጥይት የማይበገረው ልብስ እየለበሰች ትገኛለች።ከሳምንት በፊት የኮንስትሩዬ ፓርቲ ፕሬዚዳንታዊ እጩ ፈርናንዶ ቪላቪሴንሲዮ በዋና ከተማዋ ኪቶ ከምርጫ ቅስቀሳ በኋላ ሶስት ጊዜ ጭንቅላታቸው ላይ በጥይት ተመትተው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። የ36 ዓመቷ ወ/ሮ ጎንዛሌዝ የክርስቲያን ዙሪታ ተፎካካሪ በመሆን የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት እጩ ሆነው ይቀጥላሉ ።

የፈርናንዶ ራዕይ እንዲሞት አልፈቅድም ሲሉ ወይዘሮ ጎንዛሌዝ ተናግረዋል። በሚገርም ሁኔታ ጓደኛዬ መቅበር አለመቻል በጣም ከባድ ነው ስትል አክላለች። 24 ሰአት በየእለቱ ጥይት መከላከያ ልብስ እለብሳለሁ ብላለች።

የ59 አመቱ ጋዜጠኛ እና የኢኳዶር ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆነው ቪላቪሴንሲዮ ባለፈው ረቡዕ በዋና ከተማዋ ከምርጫ ቅስቀሳ ሲወጣ በጥይት ተመትቷል። ይህው ጥቃት የተፈፀመው ሬዝዳንታዊ ምርጫው ሊካሄድ 11 ቀናት ሲቀረው ነው።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *