መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 12፤2015-ኬንያዊው ወጣ በኑሮ ውድነት የተነሳ ራሱን በእሳት አቃጠለ

የኑሮ ውድነቱን በመቃወም ኬንያዊ ወጣት በትላንትናው እለት ከሰአት በኋላ በባህር ዳርቻ በምትገኘው የወደብ ከተማ ሞምባሳ ራሱን በእሳት አቃጥሏል። በህዝብ እንቅስቃሴ በተጨናነቀ ስፍራ መሀል ላይ የቆመ ሃውልት ላይ በመውጣት ራሱን አቃጥሏል።

ይፋ በተደረገ የቪዲዮ ማስረጃ ላይ እንደተመላከተው ሰውየው የኬንያ ባንዲራ ይዞ ታይቷል።ከዛም ሲጮህ፣ ትንሽ ቆይቶ፣ ትልቅ የእሳት ነበልባል ሲበላው ተመላክቷል። እሳቱን ለማጥፋት በፍጥነት በአካባቢው የነበሩ ሰዎችን ተረባርበው ታድገውታል።

የኬንያው የተቃዋሚው ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በምርጫ ከተሸነፉ በኃላ በኑሮ ውድነት እና ባለፈው አመት የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምፅ ተሰርቋል በማለት ከፍተኛ ንቅናቄ በኬንያ የፈጠረ ሲሆን ይህው ግለሰብ እንዲህ ሲናገር መስማቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል።

በምርጫው የህግ ጥሰት ነበረ የሚለው በፍርድ ቤት  ውድቅ መደረጉ ይታወሳል። ግለሰቡ በአቅራቢያው ወደሚገኝ የሞምባሳ አጠቃላይ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዶ ህክምና እየተደረገለት ይገኛል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *