
የኢራቅ ባለስልጣናት በባግዳድ ሁሉም የኤሌክትሮኒክስ ማስታወቂያ ስክሪኖች እንዲዘጉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።የበይነ መረብ መንታፊው በኢራቅ ዋና ከተማ ውስጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት መንገድ ላይ በሚገኝ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ድርጊቱ ተከስቷል።
ከክስተቱ በኃላ ቪዲዮዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው ተጋርቷል። ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል። ድርጊቱን የፈፀመው ተጠርጣሪ የማስታወቂያ ስክሪን ከሚመራው ኩባንያ ጋር ከክፍያ ጋር የተያያዘ ችግር የነበረበት ቴክኒሻን ይህንኑ ተግባር እንደፈፀመ በመግለጫው ተጠቅሷል።
የበቀል እርምጃ ስለመሆኑ ፖሊስ አስታውቋል። ቅዳሜ እለት “የኤሌክትሪክ ገመዱን በመቁረጥ ስርጭቱ እንዲቆም ከመደረጉ በፊት ዘለግ ላሉ ደቂቃዎች የወሲብ ፊልም ታይቷል” ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የደህንነት ምንጭ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል።
እነዚህ “ሥነ ምግባር የጎደላቸው ትዕይንቶች” ባለሥልጣናክ የደህንነት እርምጃ በመወሰድ “በባግዳድ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የማስታወቂያ ሰሌዳዎች እንዲጠፉ” ተደርገዋል ሲሉ አክለዋል።በዋና ከተማዋ ባግዳድ በአጠቃላይ ምርቶችን ወይም ፖለቲከኞችን የሚያስተዋውቁ ስክሪኖች እሁድ እለት ተዘግተው ውለዋል።
በስምኦን ደረጄ