መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 15፤2015-በጂንካ ከተማ ወደ ኬንያ ሊሻገሩ የነበሩ 51 ኤርትራውያን ከሶስት ደላሎች ጋር ተያዙ

በደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ከተማ በደላሎች አማካኝነት በህገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ሊሻገሩ የነበሩ 51 ሰዎች ከሶስት ደላሎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል ።
 
ፖሊስ ባደረገው ክትትል በሁለት ቀናት ውስጥ ግለሰቦቹ የተያዙ ሲሆን ሁሉም ኤርትራውያን መሆናቸው ተመላክቷል።

ከነዚህም ውስጥ ሁለቱ ህፃናት ሲሆኑ ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ክትትል ደላሎችን ጨምሮ እስከ ተሽከርካሪው እጅ ከፈንጅ መያዛቸውን የጂንካ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ሽብሩ አማረ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

አካባቢው የኬንያ ድንበር በመሆኑ ከአሁን ቀደም ይህን መሰሉ ድርጊት የተስተዋለ መሆኑንና ከ300 በላይ ሰዎች ወደ ኬንያ ለመሻገር ሲሞክሩ እንደተያዙ አንስተዋል ። በቁጥጥር የዋሉት መነሻቸውን ከአዲስ አበባ ያደረጉ መሆናቸውን ምክትል ኢንስፔክተር ሽብሩ አማረ ተናግረዋል ።

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *