
???????? 25 በአመራሮች በቁጥጥር ስር ሲዉሉ 10 ባለስልጣኖች ከወንበራቸዉ እንዲነሱ ተደርጓል
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፤ በተደረገው ማጣራት 97 ሰዎች ላይ በተለይ ከማዳበሪያ ግብዓት ጋር ተያይዘው ማስረጃዎች በማሰናዳት ለህግ እንዲቀርቡ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን ሁለት የወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ በየደረጃው ተባባሪ የሆኑ ግለሰቦችን በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል ብለዋል።
በዚህ ግምገማ መድረክ 25 ሰዎች ከብልሹ አሰራርና ከስርቆት ጋር በተያያዘ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ገልፀው በተጨማሪም 10 ከፍተኛ አመራሮች ተገምግሞ ከሃላፊነት እንዲነሱ መደረጉንም ገልፀዋል።