መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 16፤2015-በፓኪስታን በተንጠልጣይ ተሽከርካሪ(የኬብል መኪና) ላይ ባጋጠመ አደጋ ስድስት ህፃናትን ጨምሮ ስምንት ሰዎች በአየር ላይ ለሰዓታት ተንጠልጥለዋል

በፓኪስታን ሰሜናዊ ምዕራብ በሚገኝ ገደል ላይ በኬብል መኪና ውስጥ የታገቱ ስድስት ህፃናት እና ሁለት ጎልማሶችን ለማትረፍ ወታደራዊው ኃይል እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

እነዚሁ ስምንት ሰዎች  ወደ ትምህርት ቤት እያቀኑ  እያለ አንደኛው የተሽከርካሪው ገመድ ከዋናው መስመር በመለያየቱ በ274 ሜትር ከመሬት በላይ ተንጠልጥለው እንደሚገኑ ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። የፓኪስታን ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚንስትር በባታግራም በደረሰው “አስደንጋጭ” ክስተት የነፍስ አድን ሰራተኞች የተቻላቸውን በሙሉ እንዲያደርጉ አዘዋል።

ሄሊኮፕተሮች የኬብል መኪናው ያለበት ስፍራ ቢደርሱም ነየነፍስ አድን ሁኔታ ግን እጅግ አደገኛ ነው።ስምንቱ ተሳፋሪዎች የመጀመሪያው ሄሊኮፕተር ከመድረሱ በፊት ቢያንስ ለአራት ሰዓታት ያህል ታግተው እንደነበር የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ይህ  ክስተቱ ዛሬ ማለዳ በፓኪስታን አላይ ሸለቆ ላይ አጋጥሟል። የኬብል መኪናው በአየር ላይ መንጠልጠሉን የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች የድረሱላቸው ጥሪን ለመንግስት አሰምተዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *