
የብሪታንያ ፖሊስ የቀድሞ የናይጄሪያ የነዳጅ ሀብት ሚኒስትር ዲኤዛኒ አሊሰን-ማዱኬን በጉቦ ወንጀሎች መከሰሷን አስታውቋል።
የዩናይትድ ኪንግደም ብሄራዊ የወንጀል ኤጀንሲ በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የነዳጅ እና ጋዝ የስራ ውል ለመሰጠት ጉቦ እንደተቀበለች ጠርጥሬያለሁ ብሏል። የኦፔክ ፕሬዝዳንት የነበሩት ወይዘሮ አሊሰን ማዱኬ ከ2010 እስከ 2015 በቀድሞ የናይጄሪያ መሪ ጉድላክ ጆናታን አስተዳደር ውስጥ አገልግለዋል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠር ዶላር በጥሬ ገንዘብ፣ በግል አውሮፕላኖች በረራ በማድረግ፣ ከቤተሰቧ ጋር በቅንጡ ሆቴሎች የእረፍት ቀናትን ማሰለፍን ጨምሮ በርካታ የለንደን ንብረቶችን በመጠቀሟ ተጠርጥራለች።
የቀድሞ ሚኒስትሯ ክሱን ሀሰተኛ ስትል ውድቅ አድርጋለች። ፖሊስ በአሁኑ ወቅት በለንደን እንደምትኖር እና በጥቅምት ወር ፍርድ ቤት እንደምትቀርብ ተናግሯል።
በስምኦን ደረጄ