መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 22፤2015-የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት ከ4 ሺ ካርቶን በላይ የሱፍ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል ተያዘ

የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት የምግብ ዘይት ምርቱ 4 ሺ 405 ካርቶን ባለ 5 ሊትር ፈሳሽ ወይም 88 ነጥብ 1 ቶን ሲሆን ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል በአዳማ መግቢያና መውጫ ኬላ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቃል።በማዕከላዊ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በአዳማ መግቢያ መውጫ ኬላ በኩል ነሐሴ 15 ቀን 2015 ዓ.ም.በተደረገ ቁጥጥር ምርቱ መያዙ ተነግራል።

የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት ዘይት  የተመረተበት በፈረንጆቹ አቆጣጠር ግንቦት 4 ቀን 2022 ሲሆን የሚያበቃበት ጊዜ ደግሞ ግንቦት 4 ቀን 2023 መሆኑን የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበራ ደመቀ ለብስራት ሬዲዮና ቲቪ ተናግረዋል።ዘይቱ ግዜው ካለፈበት አራት ወራት አስቆጥራል።

ዘይቱ በባለስልጣን መ/ቤቱ ያልተመዘገበ ፣ከስሪት ሀገሩ የጤና ሰርተፍኬት ያልተያያዘ፣የምርቱ ገላጭ በድጋሚ የተጻፈበር ፣የምርት መለያ ቁጥር የሌለው እና በተጨማሪም በምርት ማሸጊያው ላይ ምርቱ መያዝ ያለበትን ንጥረ ነገር አለመገለጹን አቶ አበራ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በተደረገው ፍተሻ የተገኙትን ጉድለቶች መሰረት በማድረግ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባና እንዳይሰራጭ ማድረግ ተችሏል።ምርቱ ላይ በተደረገው ፍተሻ ሰፊ ጉድለቶች በመገኘቱማ የባለስልጣን መስሪቤቱ ያወጣቸውን መስፈርቶች የማያሟላ በመሆኑ በህብረተሰብ ጤና ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችል እንደነበር ተገልጿል፡፡

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *