መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 25፤2015-በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ530 በላይ ሴቶች በማህፀን በር ካንሰር ህይወታቸው ያልፋል

በዓለም ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ስርጭት ያለው የማህፀን በር ካንሰር በሽታ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ተጠቂ ማድረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጤና ሚኒስቴር የማህፀን በር ካንሰር አማካሪ የሆኑት አቶ መንግስቱ ቦጋለ ለብስራት ሬድዮና ቲቪ እንደተናገሩት ከካንሰር አይነቶች የጡት ካንሰር በኢትዮጵያ በሚያደርሰው ጉዳይ 30 በመቶ ሽፍን በመያዝ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ሲቀመጠ የማህፀን በር ካንሰር ከ13 በመቶ በላይ በመሆኑ በሁለተኛ ደረጃ ያለ የካንሰር ዓይነት መሆኑን ተናግረዋል።

በየዓመቱ 7ሺ 445  አዲስ የማህፀን በር ካንሰር ተጠቂ ሴቶች የሚመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 533 የሚሆኑት ህይወታቸው ያልፋል።የማህፀን በር ካንሰር በሽታ ከሌሎች የካንሰር አይነቶች የሚለየው መነሻው ይታወቃል ያሉን አቶ መንግስቱ መነሻውም HPV  በሚባል ቫይረስ ነው።

መነሻው መታወቁ አስቀድሞ ክትባት ለመስጠት የሚስችል እና በሽታው አስቀድሞ በመመርመር ህክምና ማድረግ ይቻላል።ሆኖም የማህፀን በር ካንሰር አስቀድም ህመም የሌለው በመሆኑ ሰዎች ቫይረሱ ተስፋፍቶ ህመም ሲጀምራቸው እና ወደ ካንሰር ከተቀየረ በኃላ ወደ ጤና ተቋም መምጣታቸው ህክምናውን አስቸገሪ አድርጎቷል።

በኢትዮጵያ 80 በመቶ የሚሆኑት የማህፀን በር ካንሰር ህመምተኞች የሚመጡት የማይድን ደረጃ ላይ ከደረሰ በኃላ ነው ።የማህፀን በር ካንሰር ያለእድሜ በሚደረግ የፆታ ግንኙነት፤ ወንዶችም ሆነ ሴቶች በፆታዊ ግንኙነት ከአንድ ሰው ጋር አለመወስን ዋና ዋና መተላለፊያ መንገዶቹ ናቸው።

የማህፀን በር ካንሰር አስቀድም ለመከላከል ከ14 ዓመት በላይ ለሆኑ  ሴቶች ክትባት እየተሰጠ ይገኛል።

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *