መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 25፤2015-ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቀሎ ለገበያ ሊቀርብ የነበረ አምስት ማዳበሪያ ቅይጥ ቂቤ ተያዘ

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በትላንትናው ዕለት ባካሂደው የገበያ ቅኝት ስራ የህብረተሰቡን ጤና ሊጎዱ የሚችሉ ቅቤን ከባዕድ ነገር እና ከአላስፈላጊ ምርቶች ጋር የተቀላቀሉ ለገበያ ሊቀርብ የነበረ አምስት ማዳበሪያ ቅይጥ ቂቤ መያዙን አስታውቋል። በተጨማሪም 691 ኪሎ ለመቀላቀያ የሚውል የአትክል ቅቤ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

በባለስልጣን መስሪያ ቤት የህዝብ እና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበራ ደመቀ ለብስራት ሬድዮና ቲቪ እንደተናገሩት ይህው የተቀላቀለ ምርት በንፋስ ስልክ ላፎቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ቻይና ካምፕ ማርያም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተይዟል።አንድ ግለሰብ አማካኝነት ንጽሕናው በተጓደለ ቤትና ቁሳቁሶች ቅቤን ከተለያዩ የዘይት ምርቶችና ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል ወደ ገበያ ለማቅረብ ሲያዘጋጅ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ሕገወጥ የቅቤ አምራቾቹን በመጠቆም ህብረተሰቡ ከፍተኛ እገዛ ያደረገ ሲሆን ባለስልጣኑ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ንፋስ ስልክ ላፎቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፣ የጀሞና አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ጋር በቅንጅት በተሰራ የቁጥጥር መያዝ መቻሉን አስታውቃል።

ይህ ምርት ከቁጥጥር ባለሙያዎች አልፎ ገቢያ ላይ ቢውል የህብረተሰቡን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ በተለይ በዓል ሲቃረብ ተመሳሳይ ሕገወጥ ድርጊቶች በስፋት የሚስተዋሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ በሚገዛቸው ምርቶች ላይ ከዚህ በፊት ከሚያውቀው የሽታ፣የጣዕም፣ የቀለምና የመጠን ለውጥ ካስተዋለ በባለስልጣኑ ነጻ የስልክ መስመር 8482 በመደወል ወይም በአቅራቢያው ለሚገኙ ፖሊሲና የጤና ተቆጣጣሪ አካላት ማሳወቅ እንዳለበት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *