መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 30፤2015-ኬንያ ወደ ሀገሯ ለሚመጣ የየትኛውም ሀገር ዜጋ ከቪዛ ነፃ ጉዞ እያሰበች መሆኑን ፕሬዝዳት ሩቶ ተናገሩ

???? ፕሬዝዳንቱ ከዚህ ቀደም የኤርትራ፣ ጁቡቲ፣ ኮሞሮስ ፣ ኢንዶኔዥያና ኮንጎ ዜጎች ላይ የቪዛ እገዳ ጥለዋል

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሀገሪቱ በጥቂት ወራት ውስጥ “ማንኛውንም የቪዛ መስፈርትን ለማንሳት በቁም ነገር እያሰበች ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ሩቶ ኬንያ የሰው ዘር መገኛ እንደሆነች ገልፀዋል፣ስለዚህም ጎብኝዎችን ወደ ቤታቸው  ሲመጡ ቪዛ መጠየቁ ፍትሃዊ አይደለም ብለዋል።

“ከተቀመጥክበት ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ሳይንቲስቶች በምድር ላይ የመጀመሪያዎቹን የሰው ልጅ ቅሪቶች አግኝተዋል፤ በሌላ አነጋገር የሰው ልጅ የጀመረው እዚህ ነው፤ ስለዚህ ወደ ቤትህ እንድቀበልህ ፍቀድልኝ አይባልም” ብለዋል። በጥቂት ወራት ውስጥ ማንኛውንም የቪዛ መስፈርት ለመሰረዝ በቁም ነገር እያሰብን ነው ምክንያቱም ወደ ቤቱ የሚመጣን ሰው ቪዛ መጠየቅ ፍትሃዊ አይደለም ሲሉ ሩቶ በትላንትናው  ዕለት በናይሮቢ የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ለአፍሪካ እና ለአለም አቀፍ መሪዎች እና ልዑካን የመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ገልፀዋል።

ሩቶ ይህንን ይበሉ እንጂ እ.ኤ.አ በመስከረም 2022 የፕሬዚዳንትነት ስልጣን ከያዙ ወዲህ ከኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ኮሞሮስ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ኢንዶኔዢያ ጨምሮ በተወሰኑ ሀገራት ላይ የቪዛ እገዳን ጥለው ቆይተዋል። ፕሬዝዳንት ሩቶ አስተዳደራቸው በአፍሪካ ህብረት ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ሀገራት የቪዛ ገደቦችን ለማስቀረት ማሰቡን ከዚህ ቀደም አስታውቆ ነበር።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *