መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 30፤2015-የክብደት መቀነሻ መድሐኒት የሚያመርተው ድርጅት በአውሮጳ እጅግ ውዱ ኩባንያ ተባለ

የክብደት መቀነሻ መድሀኒት አምራች ዌጎቪ የፈረንሳዩን የቅንጦት ምርቶች አቅራቢ ኤልቪኤምኤችን በመቀናቀን የአውሮፓ እጅግ ውዱና ጠቃሚ ኩባንያ ሆኗል። ይህው ኩባንያ ንብረትነቱ የዴንማርክ ፋርማሲዩቲካል ኖቮ ኖርዲስክ ሲሆን በእንግሊዝ ታዋቂውን የክብደት መቀነሻ መድሃኒት ማቅረብ ከጀመረ በኋላ የአክሲዮኖች ሽያጭ ጨምረዋል።

በትላንትናው እለት ግብይቱ ሲጠናቀቅ ድርጅቱ የ428 ቢሊዮን ዶላር የአክሲዮን ገበያ ዋጋ ነበረው። መድሃኒቱ በዩናይትድ ኪንግደም የህዝብ ጤና አጠባበቅ ስርዓት እና በግል ገበያ ላይም ይገኛል። ዌጎቪ በሳምንት አንድ ጊዜ የሚወሰደው ከመጠን ያለፈ ውፍረት ላለባቸው የሚሰጥ መድኃኒት ነው።

መድኃኒቱ ሰዎች ቀድመው ጠግበዋል ብለው እንዲያስቡ በማታለል በመጨረሻ ትንሽ በመብላት ክብደታቸው እንዲቀንሱ ያግዛል። ይህው መድኃኒት እ.ኤ.አ. በ 2021 በአሜሪካ ውስጥ ባሉ የጤና ተቆጣጣሪዎች ተቀባይነት ካገኘ በኋላ በሆሊውድን እና ሰፊውን የሀገሬውን ህዝብ የሳበ ሲሆን እንደ ኢሎን ማስክ ያሉ ታዋቂ ግለሰቦች እንደተጠቀሙበት ይነገራል።

ነገር ግን የጤና ባለሙያዎች መድኃኒቱ ፈጣን መፍትሄ ቢሰጥም ጤናማ አመጋገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ምትክ እንዳልሆኑ ያስጠነቅቃሉ። ተጠቃሚዎች ብዙውን ጊዜ መድኃኒቱን ካቆሙ በኋላ ክብደትን ይጨምራሉ።

አዲስ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ዌጎቪ የስትሮክ ወይም የልብ ድካም አደጋን እንደሚቀንስ ተረጋግጧል። ግን እነዚህ ግኝቶች ጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚናገሩት ባለሙያዎች ሙሉ በሙሉ መከለስ ግን ይኖርባቸዋል ይላሉ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *