መደበኛ ያልሆነ

ጳጉሜ 1፤2015-በሄሊኮፕተር ወደ ዩክሬን የሄደው ሩሲያዊው አብራሪ 500 ሺ ዶላር ሽልማት አገኘ

በኤምኣይ- 8 ሄሊኮፕተር ወደ ዩክሬን የሄደው አንድ ሩሲያዊ አብራሪ የሩሲያን ወታደራዊ መሳሪያ ይዞ ወደ ዩክሬብ በመምጣቱ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እንደሚሰጠው ተነግሯል። የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ ቃል አቀባይ አንድሪ ዩሶቭ ማክሰኞ በዩክሬን ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ገንዘቡ በብሔራዊ ምንዛሪ ሂሪቪንያ እንደሚከፈል እና ሌሎች የሩሲያ ወታደራዊ ሰራተኞችም ይህንኑ ድርጊቱ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የ28 አመቱ የሩስያ ሄሊኮፕተር አብራሪ ማክሲም ኩዝሚኖቭ ጉዳይ በዩክሬን መገናኛ ብዙሃን በስፋት ተዘግቧል። ዩሶቭ በቴሌቭዥን ባደረጉት ጥሪ የጦር ወንጀለኛ መሆን የማትፈልጉ ሩሲያውያን እባካችሁ ወደ ዩክሬን በመክዳት የራሳችሁን ክብርና ህሊና ጠብቁ፣ የሩሲያን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አገዛዝ ተዋጉ ሲሉ ጠይቀዋል።

ዩክሬንካ ፕራቭዳ የተባለው የዜና ምንጭ እንደዘገበው፣ ሩሲያዊው አብራሪ ሄሊኮፕተሯን ወደ ዩክሬን ግዛት በማብረር የዩክሬን ልዩ ሃይል እየጠበቀ በነበረበት በካርኪቭ ምስራቃዊ ክልል አርፏል።በሄሊኮፕተሩ ላይ የነበሩ ሁለት የሩስያ የበረራ ሰራተኞች የመክዳት ሴራውን ሳያውቁ እጃቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በዩክሬን ሃይሎች መገደላቸውን ዘገባዎች ጠቁመዋል።

የአውሮፕላኑ አብራሪ ቤተሰቦች ቀደም ብለው ሩሲያን ለቀው የወጡ ሲሆን በዩክሬን እንዳሉም ዘገባዎቹ ጠቁመዋል። ለዩክሬን ሀይሎች ከፍተኛ ዋጋ ያለው ኤምአይ-8 ሄሊኮፕተር ለሩስያ ተዋጊ ጄቶች መለዋወጫ ጭኖ እንደነበር ፕራቭዳ ዘግቧል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *