መደበኛ ያልሆነ

ጳጉሜ 2፤2015-በኢንዶኔዥያ ሙሽራው በሰርጉ ቀን በመቅረቱ ሙሽሪትን የሙሽራው አባት ኃላፊነቱን ወስዶ አገባ

በኢንዶኔዥያ አንዲት ሙሽሪትን በህይወቷ ውስጥ በጣም ደስተኛ በሚያደርጋት ቀን ባለቤቷ መጥፋቱን ተከትሎ ይህ ደስታ ወደ አዋራጅ ቅዠት ተለውጧል።

በኢንዶኔዥያ መገናኛ ብዙሃን እንደተዘገበው ከሆነ ኤስኤ ብቻ የተባለችው ወጣቷ በደቡብ ሃልማሄራ ጂኮታሞ መንደር ነዋሪ ስትሆን ሲሆን ከሙሽራው ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንዳላት ተነግሯል። ነገር ግን በነሀሴ 29 በሠርጋቸው ቀን ሙሽራው በመቅረቱ ለእንግዶች ስለ ሰርጉ መሰረዝ ለመናገር እጅግ አዳጋች ያደርገዋል።

ይህው ችግም በሁለቱም ቤተሰቦች ይሆናል ተብሎ የማይታሰብ የነበረ ሲሆን  ፣ ለሠርጉ ዝግጅት ገንዘብ የተከፈለ ሲሆን ለጥሎሽ ተገቢው በሙሉ በመደረጉ የሙሽራው አባት ሙሽሪትን በማግባት የስዎች ጥያቄ ዝም ለማሰኘት ሞክሯል።በኢንዶኔዥያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተሰራጨ ምስል መሰረት የሙሽሪት እና የሙሽራዋ አባቶች በአስደናቂው የሰርግ ስነስርአት ላይ አንድ ላይ ዘና ብለው ሲጫወቱ ታይ

በሰርጉ ላይ ለመታደም አስቀድመው እንግዶቹ ተገኝተዋል። የሙሽራው ቤተሰቦች ልጃቸው እንደጠፋ እና ሊገኝ እንደማይችል በማሳወቃቸው የሙሽራዋ ወንድም ዊስቶ አህመድ ለጋዜጠኞች እንደተናገረው  አባታችን ሙሽሪትን አግብቷል ሲል አረጋግጧል።

የሙሽራዋ ቤተሰብ በሙሽራው መጥፋቱ በጣም ያዘኑ ቢሆንም፣ ለሠርግ ዝግጅት ወደ 25 ሚሊዮን ሩፒያ ወይም 1,700 ዶላር ያወጡት ወጪ ሌላኛው ጭንቀታቸው ሆኗል። ዝግጅቱ ቢሰረዝ ገንዘቡን መተካት የወንዱ ሙሽራ ቤተሰብ ውጪ በመሆነ የሙሽራው አባት ማግባቱን መርጠዋል።

ይህ ያልተለመደ ሰርግ በኢንዶኔዥያ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተደበላለቀ አስተያየት የተሰጠበት ሲሆን  የወጣቷን ሙሽራ እጣ ፈንታ በርካቶች አሳዛኝ ብለውታል።አንድ አስተያየት ሰጪ የአባቴ ሚስት የቀድሞ የሴት ጓደኛዬ ናት ” ሲሉ በጉዳዩ ላይ ያጋራው መልዕክት አነጋጋሪ ሆኗል።

ይህው ጋብቻ ህጋዊ በመሆኑ ለሙሽራው እንጀራ እናቱ ሆናለች። በቀሪው ሕይወቷ ውስጥ በማትፈልገው የትዳር “ወጥመድ” ውስጥ መግባቷ የሚያስቆጭ ያሉም በርካቶች ናቸው።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *