መደበኛ ያልሆነ

ጳጉሜ 6፤2015-ሞ ፋራህ አትሌቲክስን በተሰናበተበት “ታላቁ የሰሜን ሩጫ” ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ የውድድሩ አሸናፊ ሆነ

ከብሪታኒያ የምንጊዜም ታላላቅ አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው ስመጥሩ እንግሊዛዊ አትሌት ሰር ሞ ፋራህ አትሌቲክስን በተሰናበተበት “ታላቁ የሰሜን ሩጫ” ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ ግማሽ ማራቶኑን በ59፡58 በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆኗል።

በዚህ ውድድር ከአሸናፊው አትሌት ታምራት ቶላ በ3 ደቂቃ ከ30 ሴኮንድ ዘግይቶ በ4ኛ ደረጃ የገባው ሰር ሞ ፋራህ የውድድሩ መዳረሻ በነበረው ኒውካስል ተገኝተው ሲያበረታቱት የቆዩትን ደጋፊዎቹን በክብር ተሰናብቷል።

ይህ ለኔ እጅግ በስሜት የተዋጥኩበት ሰዓት ነው፤ በአዕምሮዬ ብዙ ነገሮች ሲመላለሱ ነበር፤ የማውቀው ሙያ ሩጫ ነው፤ ላለፉት በርካታ ዓመታት ደስተኛ አድርጎ ያቆየኝም እርሱ ነው፤ ሩጫ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነው” ብሏል ሰር ሞ ፋራህ ከውድድሩ በኋላ ለቢቢሲ ተናግሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *