መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 2፤2016-ኪም ጆንግ ኡን ሩሲያ መድረሳቸውን ተከትሎ ሰሜን ኮሪያ ሁለት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈች

???? ኪም እና ፑቲን ውይይት ጀምረዋል

ሰሜን ኮሪያ የባለስቲክ ሚሳኤልን በምስራቃዊ የባህር ዳርቻዋ መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ የስታቲስቲክስ ጦር ሃይሎች ገልጿል። ምን አይነት ሚሳኤል እንደሆነ ግን እስካሁን አልተለዩም። ሰሜን ኮርያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጦር መሳሪያ ማበልፀግ መርሃ ግብሯ ላይ እገዳ ቢጥላትም ሀገሪቱ ግን በቅርብ አመታት ውስጥ በርካታ የባለስቲክ እና የክሩዝ ሚሳኤሎችን ሞክራለች።

የጃፓን ባለስልጣናትም ሰሜን ኮርያ ሚሳኤሉን ማስወንጨፉን አረጋግጠዋል። ሚሳኤሉ ከተተኮሰ በኋላ ለአምስት ደቂቃ ያህል ተጉዞ በሰሜን ኮሪያ እና በጃፓን መካከል ባለው ባህር ውስጥ መውደቁን ገልፀዋል።ይህ ሚሳኤል የተወነጨፈው ኪም ዛሬ ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው የሩስያ ፕሬዚደንት ጋር ከሚያደርጉት ስብሰባ በፊት መሆኑ አነጋጋሪ አድርጎታል።

ኪም ጆንግ ኡን ሩሲያ ሲደርሱ የቀይ ምንጣፍ አቀባበል በትናንትናው እለት በካሳን ድንበር አቋርጠው ወደ ሩሲያ ሲገቡ ተደርጎላቸዋል እንደነበር ይታወሳል።ፑቲን የሰሜን ኮሪያን መሪ ወደ ሩሲያ የላቀ የጠፈር ቦታ ሲቀበሉ “አንተን በማየቴ ደስ ብሎኛል” ሲሉ ለኪም ተናግረዋል። “ይህ የእኛ አዲሱ ኮስሞድሮም ነው” በማለት ፑቲን በ 2016 ከተከፈተው የቮስቴክኒ የጠፈር ማእከል ማስተዋወቅ አክለው ተናግረዋል።

በክሬምሊን የቴሌግራም ቻናል ላይ በወጣው ቪዲዮ መሰረት ኪም ለግብዣው ፑቲንን አመስግነዋል።ኪም ፑቲንን ሲጨብጡና ሰላምታ ሲሰጡ “በተጨናነቀ ጊዜዎ ስለጋበዙኝ አመሰግናለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *