መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 2፤2016-በሊቢያ በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ 2,300 በላይ ደረሰ

በሊቢያ ምሥራቃዊ ክፍል የምትገኘውን ዴርና የተባለችውን የወደብ ከተማ በከፊል ካጠፋው የጎርፍ አደጋ በኃላ የተገኙት አስከሬን በጅምላ ተቀብሯል። እሁድ እለት በዴርና ዳንኤል በተሰኘው ከባድ ጎርፍ ባስከተለው አደጋ የወንዞች ሙላት በመፈጠሩ ከ2,300 ሰዎች ህይወት አልፏል።

አንድ ሜካኒካል ቆፋሪ እንደተናገረው በአስክሬን ሸራ እና ብርድ ልብስ ተጎጂዎች ተጠቅልለው መቀበራቸውን ገልፀዋል። በአደጋው 10,000 ሰዎች እስካሁን ድረስ የደረሱበት ያልታወቀ ሲሆን በዚህም የተነሳ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

በዴርና ውስጥ በጎ ፈቃደኛ የሆነው መሀመድ ቃማቲ የነፍስ አድን ሰራተኞች አሁንም ተጎጂዎችን በማፈላለግ ላይ መሆናቸውን ተናግሯል።ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገረው ሁሉም ወጣት ሊቢያውያን፣ ዲግሪም ሆነ ማንኛውም የህክምና እውቀት ያለው እባካችሁ እንድትረዱን እንጠይቃለን ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

የግብፅን ጨምሮ የተወሰነ እርዳታ ሊቢያ መድረስ ጀምሯል። ነገር ግን በሊቢያ ባለው የፖለቲካ ሁኔታ ሀገሪቱ በሁለት ተቀናቃኝ መንግስታት መካከል በመከፋፈሏ የነፍስ አድን ጥረቱ ተስተጓጉሏል። አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ኢራን፣ ጣሊያን፣ ኳታር እና ቱርክ እርዳታ ልከናል ወይም ለመላክ ዝግጁ ነን ካሉ ሀገራት መካከል ይገኙበታል።

የውሃ ኢንጂነሪንግ ባለሙያዎች እንደተናገሩት ከዴርና 12 ኪሜ ርቀት ላይ ያለው ግድብ ውሃውም ወደ ሸለቆው እንዲወርድ ለማድረግ የነበረው ሂደት አለመሳካቱን በማንሳት ለከተማዋ ቅርብ የሆነው  ሁለተኛውን ግድብ ላይ ጎርፍ መጥለቅለቁ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል።የምስራቅ ሊቢያ የጤና ሚኒስትር ኦትማን አብዱልጀሊል ለአሶሼትድ ፕሬስ ከዴርና በስልክ እንደተናገሩት “የደረሰው ውድመት አስደንግጦናል ፤አደጋው በጣም ትልቅ ነው፣ከዴርና እና ከመንግስት አቅም በላይ ነው።” ሲሉ ተናግረዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *