መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 3፤2016-በህንድ አንድ ሌባ ትራክተር እየነዳ ሰርቆ ለማምለጥ መሞከሩ ተሰማ

በበይነመረብ ላይ በተሰራጨው አስገራሚ ቪዲዮ ላይ አንድ ሌባ ትራክተር ከሰረቀ በኋላ የደረሰበት እስካሁን አልታወቀም። ክስተቱ ያጋጠመው በህንድ ጉጃራት ግዛት ውስጥ ሲሆን ሌባው በትራክተር ለመስረቅ የነበረው ሂደት በካሜራ እይታ ስር ወድቋል።

በደህንነት ካሜራ ላይ ማስተዋል እንደተቻለው ግለሰቡ ትራክተሮች ወደቆሙበት  ግቢ በመግባት  የቆመ ትራክተር ለማስነሳት ሲሞክር ይታያል። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ትራክተሩ መንቀሳቀስ ይጀምራል። ነገር ግን ከትራክተሩ አጠገብ ቆሞ የሚታየው ይህ ሌባ ወደ ውስጥ ሳይገባ በተነሳድ ትራክተር የኋላ ግዙፍ ጎማ በአንዱ ተገጭቷል።

ትራክተሩ ካስነሳው በኃላ እርሱ ወደ ውስጥ ሳይገባ በራሱ መንቀሳቀስ የጀመረው ግዙፍ የግንባታ ተሽከርካሪ ሌባውን ቢገጨውም ህመሙን አፍኖ ወደ ውስጥ በመግባት ትራክተሩን ይዞ ከግቢው ወጥቷል።ትራክተሩ ጠፋ ከተባለበት ከአምስት ቀናት በኋላ ተገኝቷል።

ትራክተሩ የተገኘው ዝርፊያው ከተፈፀመበት 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነበር የሚሉ መረጃዎች ወጥተዋል። ዘራፊው ግን እስካሁን በቁጥጥር ስር ማዋል አልተቻለም። ይህንኑ ተከትሎ የህንድ ፖሊስ ግለሰቡን አድኖ ለመያዝ ተጨማሪ ምርመራ እያካሄደ ይገኛል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *