መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 9፤2016-ጀግናው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የክብር ዶክትሬት ዲግሪውን ተረከበ

በአትሌቲክስ ህይወቱ ለሀገሩ በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ እጅግ ወደር የለሽ ውጤቶችን ያስመዘገበው ጀግናው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከአርሲ ዩንቨርሲቲ ተበርክቶለት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በወቅቱ በስራ ምክንያት በአካል ተገኝቶ መቀበል ባይችልም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ተቀብለውለት የነበረ ቢሆንም የአሰላ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዱጉማ አዱኛ በተገኙበት የክብር ዶክሬቱን እና እውቅናውን  በድምቀት  በአካል  በተገኘበት ተበርክቶለታል።

የክቡር ዶ/ር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሀገሩን ወክሎ በተሳተፈባቸው ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ያስመዘገባቸው ሜዳልያዎችና ውጤቶች እስካሁን በየትኛውም አትሌት ያልተመዘገበ በመሆኑ ቀነኒሳ
በቀለን ልዩ አትሌት ያደርገዋል።

በዚህ መርሀ ግብር ላይ ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፣ ክቡር አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የአርሲ ዩንቨርሲቲ የቦርድ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች፣ አደ ስንቄዎች፣ የአትሌቱ ቤተሰቦች፣ የሙያ አጋሮቹና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *