መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 11፤2016-በቻይና ሴቶች ረጅም መስሎ ለመታየያት ሀሰተኛ እምብርት ሽያጭ መጨመሩ ተነገረ

በአሁኑ ጊዜ በቻይና በርካታ ሴቶች እግሮቻቸው ረዘም ያለ ለማስመሰል የውሸት የስቲከር እምብርታቸው ላይ እየተጠቀሙ ይገኛል።

ወጣት ሴቶች እምብርት የሚመስሉ ጊዜያዊ ንቅሳት  ከ5 እስከ 10 የቻይና ዩሃን ወይም እስከ እስከ 1 ዶላር የአሜሪካን ዶላር እየከፈሉ ነው። ተለጣፊዎቹ ሀሰተኛ እምብርቶች ብዙውን ጊዜ ከእውነተኛው እምብርት ጥቂት ሴንቲሜትር ከፍ ብለው ይቀመጣሉ።

ይህም እግሮቻቸው ረዘም ያሉ እንዲመስሉ ለማድረግ ያስችላል።በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ጊዜያዊ ንቅሳትን በመጠቀም እንዴት ረጅም መስሎ መታየት እንዳለባቸው የሚሰጡ ትምህርቶች በስፋት እየተሰራጬ ይገኛል።

እነዚህ የውሸት እምብርት ከተፈጥሯዊው ይልቅ በእይታ ማራኪ ተደርገው መሰራታቸው በበርካቶች ዘንድ ተመራጭ እየሆኑ ይገኛል። አንዳንድ ሰዎች ክብ፣ወፍራም ወይም ወደ ውጭ የወጡ ማራኪ እምብርቶችን በመለጠፍ ቁመናችንን ይበልጥ ውብ ሆኗል ሲሉ ተጠቃሚዎች ይናገራሉ።

አንዳንድ የቻይና የዜና ማሰራጫዎች ያልተጠበቀ የሆዱ ተለጣፊ ስቲከሮች ተወዳጅነት መነሻው ከቻይናውያን ባህላዊ ሕክምና ነው ሲሉ ተናግረዋል። አጠቃላይ የሰውነትን ጤንነት ለመጠበቅ የታችኛው የሆድ ክፍል ሙቀት ማግኘት አለበት ይላሉ።

የሐሰት እምብርት ለእይታ እንዲጋለጥ በማድረግ እውነተኛ እምብርትን በመደበቅ ተጠቃሚዎች ከወገብ ከፍ የሚሉ ሱሪዎች ሊለብሱ ይችላሉ።አንዳንዶች ግን በማህበራዊ ድህረ ገጽ ላይ እነዚህ የውሸት እምብርቶሽ በቻይና ማህበረሰብ ውስጥ ከእውነታው የራቀ የውበት መንገድን የሚያበረታታ ሲሉ አጣጥለውታል።

እነዚሁ ተላጣፊ እንብርቶች በቶሎ የማያረጁ እና በውሃ የማይበላሹ መሆናቸው ተነግሯል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *