መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 14፤2016-ማክሮን ፈረንሳይ ወታደሮቿን እና አምባሳደሯን ከኒጀር እንደምታስወጣ ተናገሩ

????የኒጀር መንግስት የፈረንሳይን መውጣት በደስታ እጠብቃለሁ ብሏል

ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መፈንቅለ መንግስቱን ተከትሎ ፈረንሳይ አምባሳደሯን እንደምታስወጣ እና ከኒጀር ጋር የነበራትን ወታደራዊ ትብብር እንደምታቆም ተናግረዋል። ማክሮን “ፈረንሳይ አምባሳደሯን ለማስወጣት ወስናለች ፤በሚቀጥሉት ሰዓታት የእኛ አምባሳደር እና በርካታ ዲፕሎማቶች ወደ ፈረንሳይ ይመለሳሉ” ብለዋል ። አክለውም ወታደራዊ ትብብር “አልቋል” እናም የፈረንሳይ ወታደሮች “በቀጣዮቹ ወራት” ውስጥ ኒጀርን ለቀው እንደሚወጡ ተናግረዋል።

በሀምሌ ወር ኒጀር ውስጥ ስልጣን የተቆጣጠረው ወታደራዊ መንግስት እርምጃውን በደስታ እንደሚቀበል ገልጿል። ” ለኒጀር ሉዓላዊነት አዲስ እርምጃ ነው ብለን ቀኑን እናከብራለን” ሲል ወታደራዊው አገዛዝ መግለጫ ማውጣቱን አጃንስ ፍራንስ ፕሬዝ የዜና ወኪል መግለጫውን ጠቅሶ ዘግቧል። ወደብ አልባ በሆነችው የምዕራብ አፍሪካ ሀገር ኒጀር ወደ 1,500 የሚጠጉ የፈረንሳይ ወታደሮች ይገኛሉ።

የፓሪስ ውሳኔ ለወራት የዘለቀው የፈረንሳይ ጥላቻ እና  የተቃውሞ ሰልፍ በዋና ከተማዋ ኒያሚ ሲደረግ የነበረው ሁኔታ ማብቂያ በመሆኑ ለነዋሪዎች ደስታን ሰጥቷል። ርምጃው ፈረንሳይ በሰፊው የሳህል ክልል ታጣቂዎች ላይ የምታካሂደውም የጦር ዘመቻ ላይ ተፅእኖ ሊፈጥር ይችላል።

ማክሮን አሁንም በመፈንቅለ መንግስቱ መሪዎች በእስር ላይ የሚገኙትን ከስልጣን የተባረሩትን የኒጀር ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ባዙምን የሀገሪቱ ብቸኛ ህጋዊ ፕሬዝዳንት አድርገው እንደሚቆጥሩ ተናግረዋል። ከስልጣን የተነሱትን ፕሬዝዳንት “ታጋች” ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *