
በሳውዲ አረቢያ አንድ ሌባ በባለቤቱ አፍንጫ ስር መኪናውን ሲሰርቅ የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ እየተሰራጨ ይገኛል። የሳውዲ አረቢያ የዜና ወኪል እንደዘገበው ድርጊቱ በደማም መከሰቱን ዘግቧል።
ይህው ቪዲዮ እንዳመላከተው የመኪናው ባለቤት ሞተሩ ላይ ባጋጠመው እክል ከተሽከርካሪው ወርዶ በጥገና ስራ ላይ እያለ ሌባው ከሌላ አቅጣጫ ሲመጣ ይታያል። ሌባው ተደብቆ በመምጣት ተሽከርካሪውን አስነስቶ ሲሸሽ ይታያል።
የመኪናው ባለቤት ሌባውን ለመያዝ ቢሞክርም ጥረቱም ከንቱ ሆኗል። ወንጀለኛው የመኪናውን ኮፈን ክፍት አድርጎ ሸሽቷል። በኋላ ላይ ፖሊስ ሌባውን በቁጥጥር ስር በማዋል ተሽከርካሪውን ለባለቤቱ አስረክቧል።ህጋዊ ሂደቱ መቀጠሉን የሳዑዲ አረቢያ ፖሊስ አስታውቋል።
በስምኦን ደረጄ