መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 14፤2016-ከባንክ 35 ሺህ ብር ሰርቆ ሮጦ ለማምለጥ የሞከረዉ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በጋምቤላ ክልል ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜጢ ቅርንጫፍ በመግባት 35,000 ብር ይዞ  የሮጠው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጎደሬ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች  ጽ/ቤት አሳዉቋል።

ግለሰቡ ወደ ባንኩ ከገባ በኋላ ብር ለማውጣት ወጭ የሚጠይቅ አስመስሎ ለሌላ ሰው የተቀመጠውን 35 ሺህ ብር ከጠረጴዛ አንስቶ ሲሮጥ በፀጥታ ሀይሎችና በባንኩ ጥበቃ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋሉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ግለሰቡ አራት መታወቂያ እና የሌላ ሀገር የገንዘብ ኖት ከኪሱ የተገኘ ሲሆን በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት እንዳለም ለማወቅ ተችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *