መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 18፤2016 -በሌቦች ተሰርቃ ለእርድ የተጀመረች ፍየል ወደ እንስሳት ህክምና መወሰዷ ተነገረ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በከፋ ዞን በጊምቦ ወረዳ መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ጡላ ቀበሌ መሀል ጡላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሁለት ግለሰቦች አንድ ፍየል እና አንድ በግ ከታሰሩበት ሰርቀዉ መዉሰዳቸዉን ተገልጿል ።

ሁለቱ ሌቦቹ ሰርቀዉ ከወሰዱ በኋላ ፍየሏን በማረድ ላይ እያሉ የአከባቢዉ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸዉን ከበዉ በማረድ ላይ የነበሩትን ፍየል ማስጣላቸው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በዚህም መሰሠረት ለእርድ አንገቷ  የተቆረጠችዉን ፍየል ወደ እንስሳት ህክምና የተወሰደች መሆኑንና የስርቆት ወንጀል ፈፃሚዎች ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንደተወሰዱ አክለዋል ። ፍየሏ ወደ እንስሳት ህክምና ከተወረደች በኋላ ህክምና ተደርጎላት በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች ተብሏል ።

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *