መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 18፤2016 – የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ ሁለት ሴቶች በከሰል ጭስ ህይወታቸው አለፈ

???? የመዉሊድ፣ የደመራና የመስቀል በዓል ላይ የእሳት አደጋ አለመከሰቱ ተነግሯል

በአዲስ አበባ ከተማ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሁለት ሴቶች በከሰል ጭስ ታፍነዉ ህይወታቸው ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንና አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴለቪዥን እንደተናገሩት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታዉ ሰኔ ዘጠኝ ትምህርት ቤት ጀርባ ባለ መኖሪያ ቤት ዕድሜያቸዉ 35 እና 39 የሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ ሁለት ሴቶች በከሰል ጢስ ታፍነዉ ህይወታቸዉ አልፏል ።

ህይወታቸዉ ባለፈበት ቤት ዉስጥ ጢሱን ያልጨረሰ ከሰል በማሰገባት በር ዘግተዉ በመተኛታቸዉ ሁለቱም ሰዎች በተኙበት ህይወታቸዉ አልፏል።

በሌላ በኩል የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከበዓላቱ አስቀድሞ በተለያዩ አማራጮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት ከበዓላቱ አስተባባሪዎችና ከሀይማኖት አባቶች እንዲሁም ከጸጥታ ሀይሎች ጋር በጋራ በመሰራቱ በዓላቱ ያለእሳት አደጋ ክስተት በሰላም መጠናቀቅ መቻሉን አቶ ንጋቱ ጨምረዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

በትግስት ላቀዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *