
ለሁለት አመት በፈጀ የሆድ ህመም ሲሰቃይ የነበረው ግለሰብ በሆዱ ውስጥ ከቁልፍ እስከ ጆሮ ማዳመጫ የሚደርሱ የቤት እቃዎች መገኘኙ የህክምና ባለሙያዎችን አስደንግጧል። በሞጋ ፑንጃብ ነዋሪ የሆነ ይህው ግለሰብ ላይ ምርመራ ያደረጉት የሞጋ ሆስፒታል ዳይሬክተር አጅመር ሲንግ ካልራ እንደተናገሩት “በኤክስሬይ ምርመራ ወቅት ሰንሰለት፣ ቁልፍ፣ የጆሮ ማዳመጫዎች እና ሌሎች በርካታ ቁሶችን በሆድ ውስጥ አገኘን” ሲሉ ተናግረዋል።
የ35 ዓመቱ ታካሚ ኩልዲፕ ሲንግ በደረሰበት የሆድ ህመም እና ከፍተኛ ትኩሳት ምክንያት ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ነበር። የሕክምና ባለሙያዎች የችግሩን ባደረጉት የቀዶ ህክምና ከሲንግ ሆድ ውስጥ ሰንሰለቶች ፣ብሎኖች ፣ የጆሮ ማዳመጫዎች ፣ የደህንነት ፒን ፣ ማግኔቶች ፣ የሸሚዝ ቁልፎች እና ዚፖች እና ሌሎች ወደ 60 የሚጠጉ ቁሳቁሶችን አውጥተዋል።
እንዲህ ዓይነት ልምድ በትናንሽ ህጻናት፣ አንዳንዴ በነፍሰ ጡር ሴቶች እና እንደ ኦቲዝም እና ስኪዞፈሪንያ ባሉ የአእምሮ ህመምተኞች ላይ የተለመዱ ናቸው።
የማይፈጩ ነገሮችን መብላት ለጤና አደገኛ ነው ያሉት የህክምና ባለሙያዎቹ ሲንግ ሹል እና ስለታማ ነገሮችን ስለዋጠ በሆዱ ላይ ከባድ ቁስሎች ነበሩ ለዚህም ቀዶ ህክምና ለማድረግ ወስነናል ብለዋል። የቀዶ ህክምናው ሂደት ሶስት ሰዓታትን ጠይቋል።
በስምኦን ደረጄ