መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 21፤2016 – ካታሊን ካሪኮ እና ድሩ ዌይስማን ለኮቪድ ክትባት በመስራታቸው በሕክምና ዘርፍ የኖቤል ሽልማትን አሸነፉ

የሃንጋሪ ተወላጅ የሆነችው ካታሊን ካሪኮ እና አሜሪካዊው ድሩ ዌይስማን የ2023 የኖቤል ሽልማት በፊዚዮሎጂ ወይም በህክምና ዘርፍ አሸንፊ ሆነዋል።በፊዚዮሎጂ ወይም በህክምና ዘርፍ አሸናፊ የሆኑት በኮቪድ ወረርሽን ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ የኤም አር ኤን ኤ ክትባቶችን በመስራታቸው ሲሆኑ ክትባቱ በፋይዘር እና ሞደርና መቅረቡ ይታወሳል።

በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በዛሬው የሽልማት ድርጅቱ እንዳስታወቀው  “ተሸላሚዎቹ በዘመናዊው ዓለን በሰው ልጅ ጤና ላይ ከፍተኛ ሥጋት የደቀነውን ወረርሽን ለመዋጋት ከፍተኛ የክትባት ምርምር ሂደት ላይ አስተዋጽዖ አበርክተዋል” ብሏል።ካታሊን ካሪኮ በሃንጋሪ የሳጋን ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር እና በፔንስልቬንያ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ናይ።

ድሩ ዌይስማን በፔንስልቬንያ ዩኒቨርሲቲ ከካሪኮ ጋር በመሆን የምርምሩን ሂደት አካሂደዋል። ሁለቱ ተሸላሚዎች ሽልማታቸውን  በአልፍሬድ ኖቤል የህልፈት ቀን በ1896 ታህሳስ 10 ቀን በስቶክሆልም በሚካሄደው መደበኛ ሥነ-ሥርዓት ላይ ዲፕሎማ፣ የወርቅ ሜዳሊያ እና የ1ሚሊዮን ዶላር ቼክ ከንጉሥ ካርል 16ኛ ጉስታፍ እጅ ይቀበላሉ።

የኖቤል ፊዚክስ ተሸላሚ ማነው የሚለው በነገው እለት ማክሰኞ የሚታወቅ ሲሆን የኬሚስትሪ ረቡዕ እንዲሁም የስነ-ጽሁፍ ተሸላሚ ሐሙስ እለት ይፋ ይሆናል። የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ አርብ የሚታወቅ ሲሆን የኢኮኖሚክስ ተሸላሚ ደግሞ የዛሬ ሳምንት ሰኞ ይፋ ይደረጋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *