መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 22፤2016-መስጊድ ውስጥ በመግባት ከሶላት ሰጋጆች ጫማ የሰረቀው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በጅማ ዞን ኦሞናዳ ወረዳ 01 ቀበሌ  መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም በጅማ ዕለት ከቀኑ 6 ሰዓት ከሶላት ሰጋጆች ጫማ ሰርቆ ለመሰወር የሞከረ ግለሰብ በአስቸኳይ ችሎት በእስራት መቀጣቱ ተገልጿል ።

ተከሳሹ ጀማል ሙዲ የሚባል ሲሆን መስጊድ ውስጥ የሰረቀውን ጫማ ይዞ ለመሰወር ሲሞክር እጅ ከፈንጅ መያዙን የኦሞናዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ምስክር ጌታቸው ለብስራት ራዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ፖሊስ ያጣራውን የምርመራ መዝገብ የተቀበለው አቃቤ ህግ ለኦሞናዳ ወረዳ ፍርድ ቤት የክስ መዝገቡን አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል ። በዚህ መሠረት ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ጀማል ሙዲ አንድ ዓመት ከስድስት ወር እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል ።

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *