መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 22፤2016-የግብፁ ፕሬዝዳንት ኤል-ሲሲ ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን ይወዳደራሉ መባሉን ተከትሎ ተቃዋሚዎች ቁጣቸውን ገለፁ

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ በታህሳስ ወር ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ ለሶስተኛ ጊዜ የስልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ አረጋግጠዋል። ኤል ሲሲ ያሸንፋሉ ተብሎ በሚጠበቀው የግብፅ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ  በኢኮኖሚ ቀውስ ፣የዋጋ ግሽበት ፣በከፍተኛ ደረጃ የወረደ የሀገር ውስጥ ምንዛሪ እና የፖለቲካ ተቃዋሚዎቿ እጩዎቿ ትንኮሳ እና ማስፈራራት እየደረሰባቸው ባለበት ወቅት የሚደረግ ምርጫ መሆኑ ተገልጿል።

ኤል-ሲሲ ሰኞ አመሻሽ ላይ በግብፅ ብሄራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈ መግለጫቸው ላይ ” የጀመርኳቸውን ህልሞቼን ለመጨረስ ለአዲስ የፕሬዚዳንትነት ዘመን እራሴን ለመሾም ወስኛለሁ” ሲሉ ተናግረዋል። “ሁሉም ግብፃውያን በዚህ ዲሞክራሲያዊ መድረክ እንዲሳተፉ ሀገር ወዳድ እና ለምርጫ ብቁ የሆኑ ሁሉ እንዲመርጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ሲሉ አክለዋል።

ከታህሳስ 10 እስከ 12 ባለው ጊዜ ውስጥ ለሶስት ቀናት በሚቆየው ምርጫ 65 ሚሊዮን የሚገመቱ ግብፃውያን ድምጽ ሊሰጡ እንደሚችሉ ተነግሯል።በ ውጭ ሀገራት የሚኖሩ ግብፃውያን ከታህሳስ 1 እከ 3 ቀን ድምጽ ይሰጣሉ።ጥቂት የማይባሉ ፖለቲከኞች ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ ቢያሳውቁም እ.ኤ.አ. ከ2014 ጀምሮ በስልጣን ላይ የሚገኙትን ኤል-ሲሲን ያሸንፋሉ ተብሎ ግን አይጠበቅም።

የሙስሊም ወንድማማቾች ብራዘርሁድ መሪ በግብፅ ለመጀመርያ ጊዜ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡትን ፕሬዝደንት መሀመድ ሙርሲን ከስልጣን አልሲሲ በኃይል በማስወገድ ስልጣን መያዛቸው ይታወሳል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *