
አዲስ በየነ የተሰኘች ኢትዮጵያዊት ትሰራበት ከነበረችበት ቤት የ4 ዓመት ዶሞዝ ሳይከፈላት እንደቆየ በባህሬን ለሚገኘዉ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ሪፖርት ማድረጓን ቆንስላዉ ገልጿል።
ይህንን ተከትሎም ጽ/ቤቱ ከባህሬን የሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር በመነጋገር ሙሉ ደሞዟ እንዲከፈላት ማድረጉን አሳዉቋል።
ግለሰቧም ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በዝግጅት ላይ ትገኛለች መባሉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን በባህሬን ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል።