መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 23፤2016 – የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬቨን ማካርቲ ከስልጣን እንዲወርዱ ድምጽ ሰጠ

ኬቨን ማካርቲ በቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች ተቃውሞ የተነሳ ከስልጣናቸው ተወግደዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የመተማመኛ ድምፅ ሲያጣ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የካሊፎርኒያ ኮንግረስማን የሆኑት ኬቨን ማካርቲ በታችኛው የኮንግረስ ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ 216 በ210 በሆነ ውጤት የመተማመኛ ድምፅ አጥተዋል።

ማካርቲን ከስልጣን ለማስወገድ ጥረቱን የጀመሩት የቀኝ አክራሪው የፍሎሪዳ ኮንግረስማን ማት ጌትዝ ሲሆኑ ድምጽ ከመሰጠቱ በፊት በማህበራዊ ሚዲያ ድህረ ገጽ ላይ አፈ ጉባኤ ማካርቲ አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ላይ አቋም መያዝ አልቻሉም ብለዋል። “ስለዚህ እሱ ካልፈቀደ እኔ አደርገዋለሁ” ሲሉ አክለዋል።

ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልከ በጥር ወር አፈ-ጉባኤ ከሆኑበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ አጋጣሚዎች በማካርቲ የስልጣን ዘመን የሪፐብሊካን ፓርቲ ውስጥ ብጥብጥ እየጨመረ መጥቷል።በፓርቲው ውስጥ ማካርቲን ለመተካት ምንም ግልጽ ምርጫ እስካሁን የለም።ማክሰኞ ማምሻውን በተደረገው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ስምንት ሪፐብሊካኖች ለአፈ ጉባኤው ድምፅ ባለመስጠታቻው ስራቸውን ለማስቀጠል የሚያስፈልጋቸውን አብላጫውን የማረጋገጥ እድላቸውን አሳጥተዋል።

የዋይት ሀውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ካሪን ዣን ፒየር እንደተናገሩት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ምክር ቤቱ አዲስ አፈ-ጉባኤን በፍጥነት እንደሚመርጥ ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል።ለማይክ ካርቲ ከስልጣን ለመወገዳቸው ምክንያቱ በራሳቻው ሪፐብሊካን ፓርቲ ውስጥ የሚፈጠረው የውስጥ ሽኩቻ ተከትሎ ባጋጠማቻው ውሳኔ የመስጠት ተግዳሮት ነው።በድጋሚ ለአፈ ጉባኤነት እንደማይወዳደሩ አስታውቀዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *