መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 24፤2016 – በምስራት ቦረና ዞን ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ካናቢስ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ዋለ

በምስራቅ ቦረና ዞን በዋጫሌ ወረዳ ግምታዊ ዋጋው ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ካናቢስ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል ።

ካናቢስ የተባለው አደንዛዥ እፅ ከሻሸመኔ ከተማ ወደ ዋጫሌ ወረዳ ለማስገባት ሲሞከር መያዙን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኦዳ ገናሊ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ። በቁጥጥር የዋለው አደንዛዥ እፅ ህብረተሰቡ በተገኘበት እንዲቃጠል መደረጉን አክለዋል ።

በሌላ በኩል በምስራቅ ወለጋ ዞን በዲቻ ወረዳ 55 ሺህ ሀሰተኛ የብር ኖት ከሁለት ግለሰቦች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል ። ሁለቱ ግለሰቦች የያዙት አጠቃላይ ድምሩ 55 ሺህ የሆነ ባለ 200 ሀሰተኛ የብር ኖት ጨምሮ በመዘርዘር ሊገለገሉበት በእንቅስቃሴ ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዲቻ ወረዳ ፖሊስ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ኦፊሰር ሳጂን ደምሲ ዲንሳ ተናግረዋል ።

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *