
አንድ የኒው ጀርሲ ሰው ሆን ብሎ ተሽከርካሪውን ወደ መኖሪያ ቤት እና ፖሊስ ዲፓርትመንት ቢሮ ላይ ማጋጨቱን የከተማው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። በአደጋው ማንም አልተጎዳም ሲሉ የዋረን ካውንቲ አቃቤ ህግ ቢሮ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ይሁን እንጂ የ34 ዓመቱ የቤልቪዲሬ ከተማ ነዋሪ ጆን ሃርግሬቭስ በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት በመኪና ጥሶ ሲገባ አንድ የፖለስ መኮንን ከአደጋው ለጥቂት አምልጧል።
አቃቤ ህግ እንዳስታወቀው ተከሳሹ አደጋውን ካደረሰ በኃላ እጆቹን እያውለበለበ በጀግንነት ስሜት Guns N’ Roses የሚለው ዘፈን ጮክ ብሎ ሲጫወት ነበር ብሏል።ሃርግሬቭስ በሁለቱም አደጋዎች በስርቆት፣ በወንጀል ክስ እና በመሳሪያ መያዝ በሚል ተከሷል።
እንዲሁም በፖሊስ ጣቢያ ላይ ባደረሰው አደጋ ምክንያት ባሽብርተኝነት፣የከፋ ጥቃት እና ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ በሚሉ ወንጀሎች ይከሰሳል። ባለስልጣናቱ ለአደጋው መንስኤ ሊሆን የሚችልበትን ምክንያት አልገለጹም።
በስምኦን ደረጄ