በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት ከቀኑ 6 ሰዓት ከ20 ገዳማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 መሿለኪያ ጤና ጣቢያ አካባቢ በአንድ ቪላ መኖሪያ ቤት ላይ የተነሳው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የእሳት አደጋዉ በአንድ ግለሰብ ቪላ መኖሪያ ቤት ላይ የደረሰ ሲሆን በእሳት አደጋዉ 3.5 ሚሊየን የሚገመት ንብረት መውደሙን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።የእሳት አደጋዉ የተነሳዉ በቤት ዉስጥ ተለኩሶ በተረሳ ሻማ ምክንያት ነው።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አራት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ከ29 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ተሰማርተዋል። አደጋዉን ለመቆጣጠር በተደረገ ጥረት በአቅራቢያዉ ባሉ ህንጻዎች ሳይዛመት በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለ ሲሆን በዚህ ሂደት 150 ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት ማዳን ተችሏል።
በእሳት አደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።
በትግስት ላቀ