መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 24፤2016 – በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት ቦይለር ፈንድቶ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት ከቀኑ 10:35 ሰዓት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የቀድሞ አቃቂ ጨረቃ ጨርቅ ጊቢ ዉስጥ በሚገኝ ሶሻል ሳሙናና ኘላስቲክ ፋብሪካ ዉስጥ የዉሀ ማሞቂያ ቦይለር ፈንድቶ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ለጊዜዉ ቁጥራቸዉ በውል ያልታወቀ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተመላክቷል።ህይወታቸዉ ያለፈው እና በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸዉ ሰዎች የፋብሪካዉ ሰራተኞች መሆናቸውን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ጉዳት የደረሰባቸዉ ተጎጂዎች በአንቡላንስ ወደ ህክምና ተቋም ተወስደዋል።

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *