
በስጤ ዞን ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ወሊያ ቀበሌ ልዩ ስሙ አውዘኜ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ከአንድ የግል ተበዳይ ማሳ ዉስጥ ዘልቀዉ በመግባት ነው ስርቆቱን የፈፀሙት።
አብዱልዋሂድ ፈድሉ፣ ሙኒር ፈድሉ፣ አብዱልወኪል ዘይኔ፣ የተባሉት ሶስቱ ተከሳሾች ሐምሌ 04 ቀን 2015 ዓ.ም ንጋቱ 12: 00 ግድም ከግል ተበዳይ ማሳ ዉስጥ ጫት ሰብረዉ በመዉሰድ ስርቆት መፈፀማቸዉ በማስረጃ መረጋገጡን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ።
ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ባደረገዉ ማጣራት ተከሳሾችን በመያዝ ያጣራዉን የምርመራ መዝገቡን ለዓቃቢ ህግ በመስጠት ዓቃቢ ህግም ለምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ በመመስረት የተከሳሾቹ ጥፋተኝነት በማስረጃ አረጋግጧል ብለዋል ።
የወንጀል ችሎትም ሶስቱን ተከሳሾች እያንዳንዳቸዉ በሶስት ዓመት ከሶስት ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በምህረት ታደሰ