መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 24፤2016-የሄይቲ ቀውስ የኬንያ ቀዳሚ ጉዳይ አይደለም “በቂ ችግር አለን” ሲሉ ራይላ ኦዲንጋ ተናገሩ

የኬንያ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ኬንያ በሄይቲ የሚገኘውን የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለመምራት እና የወሮበሎች ጥቃት ለመከላከል መወሰኗን “የተሳሳተ እርምጃ” ሲሉ ተናግረዋል።

ኦዲንጋ ከኬንያ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በሄይቲ ፖሊስ ለማሰማራት የታቀደው የኬንያ ቀዳሚ ጉዳይ እንዳልሆነ ገልጸው፣ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ቀድሞውንም “በቂ ችግር” እንደነበረበት ተናግረዋል። “ወደ አፍሪካ ለመፍትሄ ከመምጣትህ በፊት ሄይቲ በአለም ላይ እጅግ ኃያል ከሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ ደጃፍ ላይ የምትገኝ ሀገር ናት ብለዋል።

በሄይቲ የሚገኘውን ሁለገብ የወንበዴ ቡድንን ለመደምሰስ ኬንያ የምትመረጠው ልዩ የሆነ ምን ነገር አላት ሲሉ ኦዲንጋ ተናግረዋል። በሄይቲ ያለው ሁኔታ አደገኛ መሆኑን ኦዲንጋ በመግለጽ፣ የታቀደው የሥምሪት እርምጃ የኬንያ ፖሊስን ሕይወት አደጋ ላይ እንደሚጥል አስጠንቅቀዋል። “የሬሳ ሣጥኖች እዚህ መድረስ ሲጀምሩ ያኔ መቆጨት እንጀምራለን ሲሉ አክለዋል።

ሄይቲ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነች እና ፖሊሶቻችን እዚያ ችግር ሊገጥማቸው የሚችልበት እድል አለ ብለዋል። ኦዲንጋ አክለውም “በሄይቲ ያለው ችግር ፖለቲካዊ ነው፣ ጠመንጃ ብቻ ሳይሆን መነጋገርን ይጠይቃል።

ሰኞ እለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ከዘጠኝ ወራት በኋላ ባደረገው ግምገማ ለአንድ አመት በኬንያ የሚመራው ኃይል በሄይቲ እንዲሰማራ አፅድቋል። የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ “የሄይቲን ህዝብ ላለማሳደድ” ቃል ገብተዋል። ይሁን እንጂ አንዳንድ ተቺዎች የኬንያ ፖሊሶች የሄይቲን ወንጀለኞች ለመያዝ ያላቸውን አቅም ጥርጣሬ በመግለጽ እርምጃውብ ተቃውመውታል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *