መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 25፤2016 – ሴኔጋል በቲክ ቶክ ላይ የጣለችውን እገዳ እንደምታራዝም አስታወቀች

የሴኔጋል መንግስት በነሀሴ ወር በቲክ ቶክ የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ ላይ የጣለውን እገዳ እንደሚያራዝም አስታውቋል።

የሴኔጋል ባለስልጣናት መተግበሪያውን “የሀገሪቱን መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥሉ የጥላቻ እና ሃገርን የሚያፈርሱ መልዕክቶችን ለማሰራጨት ተንኮል-አዘል ሰዎች የተቆጣጠሩት አውታረ መረብ ነው” በሚል ክስ አግደውት ነበር። የሴኔጋል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ሙሳ ቦካር ቲያክቶ ቲክቶክ ወደነበረበት መመለስ የሚቻለው ኩባንያው ግጭት ፈጣሪ ይዘቶችን የሚያስተዋውቁ ሂሳቦችን ለማስወገድ ስምምነት ከፈረመ ብቻ ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ ቲያም ከኩባንያው ተወካዮች ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ “ለጊዜው እገዳው እንደተጠበቀ ነው ብለዋል። እገዳው ሊነሳ የሚችለው አጠቃላይ የጽሁፍ ስምምነት ላይ ሲደረስ ነው ሲሉ አክለዋል።” የቲክ ቶክ እገዳ የተቃዋሚ መሪ ኦስማን ሶንኮ መታሰርን ተከትሎ ነው።

ሶንኮ በቁጥጥር ስር ውለው ሁከትና ብጥብጥ በተነሳበት ወቅት መተግበሪያው የሀገሪቱን መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥሉ “የጥላቻ እና አፍራሽ መልዕክቶችን” ለማሰራጨት ጥቅም ላይ ውሏላ  ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል። መንግስት ቲክ ቶክን ወደነበረበት ለመመለስ የሴኔጋል ይዘት ፈጣሪዎችን ፍትሃዊ ካሳ ለመስጠት እንዲስማማ ኩባንያውን ጠይቋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *