መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 25፤2016- በህንድ የስምንት ዓመቷ ልጅ በቤተሰቡ ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ “አባቷን ይሸጣል” የሚል ፖስተር ማስለጠፏ መነጋገሪያ ሆኗል

በህንድ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በስፋት እየተሰራጨ ባለው መረጃ መሰረት በቤት ውስጥ የተፈጠረ አለመግባባት ተከትሎ አንዲት የስምንት አመት ልጅ አባቷን ለመሸጥ ሞክራለች። ይህንኑ የሚገልፅ ፖስተር በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቷል።

አንዲት የስምንት ዓመት ልጅ አባቷን ለሽያጭ በማቅረብ በቤት ውስጥ በተፈጠረ መጠነኛ አለመግባባት አባቷን ለማስወገድ ሞክራለች። በእጅ የተጻፈው ፖስተር በቀድሞ ትዊተር  በአሁኑ ኤክስ ላይ  ተጋርቷል።  “በ 2 መቶ ሺ ሩፒ አባቷ እንደሚሸጥ በመግለፅ ለበለጠ መረጃ መደወል ይቻላል” ይላል።

በመጠነኛ አለመግባባት የ8 አመቷ ልጅ ከምትኖርበት አፓርትማ በር ላይ ለሽያጭ አባቷን ማቅረቧን ኢንዲያን ታይምስ ዘግቧል።መረጃው ከተጋራ በኃላ የተለያዩ አስተያየቶች ተደምጠዋል። አንድ ግለሰብ በሰነሰረው አስተያየት “ልጅቷ ከዚህ በፊት እንደዚህ ዓይነት ድርጊት ካላጋጠማት በስተቀር አንድ ልጅ ወላጁን ይቅርና ማንንም ሰው “ልሸ” ብሎ ማሰብ ይችላል? እኔ ይህንን ማየት ተስኖኛል” ሲል ገልጿል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *