መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 25፤2016-በአፄ ቴዎድሮስ መኝታ ራስጌ ላይ ይሰቀል ነበር የተባለዉ የእየሱስ ክርስቶስ ምስዕል በእንግሊዝ ተገኘ

500 አመታት እድሜ እንዳለዉ የሚገመተዉና በአፄ ቴዎድሮስ መኝታ ራስጌ ላይ ይሰቀል ነበር የተባለዉ የእየሱስ ክርስቶስ ምስዕል በእንግሊዝ መገኘቱ ተነግሯል።

በመቅደላ ጦርነት ወቅት ከኢትዮጵያ ጥንታዊ የብራና ጽሁፎችና እና ቅርሶችን እንዲያመጣ ከእንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ በተላከዉ የብሪቲሽ ሙዚየም ባለሙያ ሪቻርድ ሆምስ የተሰረቁ መሆናቸዉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። ግለሰቡ የተለያዩ ቅርሶችን ለእናት ድርጅቱ ካስረከበ በኋላ የእየሱስ ክርስቶስን ምስዕል ግን ለራሱ አስቀርቷል ነዉ የተባለዉ። ከቆይታዎች በኋላም እ.ኤ.አ በ1917 ለሌላ አካል ሸጦት ነበር ተበሏል።

ምስዕሉ በፖርቱጋል ቁጥጥር ስር ከሆነ በኋላም ከእይታ ተሰዉሮ ነበር ተብሏል። እ.ኤ.አ በ1520 ተስሏል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ከደረሰ በኋላ በግዕዝ ቋንቋ ተጨማሪ ገለጻ ተጽፎበታል። ከነገሥታት ወደ ነገሥታት በቅብብሎሽ ሲተላለፍም ነበር ተብሏል።

ከሐር በተሸመነ ጨርቅ ላይ ባረፈዉ ስዕል የወቅቱ የብሪቲሽ ሙዚየም ባለሙያ በእጅ ጽሁፉ መቅደላ ሚያዚያ 13 ቀን 1868 የሚል ጽሁፍ ተገኝቶበታልም ተብሏል። ይህም ከኢትዮጵያ ምስዕሉን ያገኘበት ወቅት ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል ሲል ብስራት ሬዲዮና ቲቪ ዘግቧል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *