መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 28፤2016–የጸጥታው ምክር ቤት በአሜሪካ በኩል ሃማስን ለማውገዝ የቀረበው ጥሪ ስምምነት ላይ መድረስ ሳይችል ቀረ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በእስራኤል እና በሀማስ ጦርነት መካከል ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በዝግ በሮች ተገናኝቶ የነበረ ቢሆንም ለጋራ መግለጫ የሚያስፈልገውን የአንድነት ሀሳብ ማምጣት ግን አልቻለም።

ዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤቱን 15 አባላት ሃማስን አጥብቀው እንዲያወግዙ ጠይቃለች። ነገር ግን ዲፕሎማቶች በሩሲያ የሚመሩት አባላት የፍልስጤምን ታጣቂ ቡድን ከማውገዝ ይልቅ ሰፋ ያለ ትኩረት እንደሚሰጡ ገልፀዋል። ምክር ቤቱ ለ90 ደቂቃ ያህል ተሰብስቦ የነበረ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም መልዕክተኛ ቶር ዌንስላንድን አጭር መግለጫ አቅርበዋል።

የሐማስ ከፍተኛ ባለስልጣን ቡድኑ በእስራኤል ላይ ካደረሰው ጥቃት በኋላ ከ100 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። ሙሳ አቡ ማርዙክ እሁድ እለት ለአረብኛ ቋንቋ የዜና አውታር አል-ጋድ በሰጡት አስተያየት “የእስራኤል ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ይገኙበታል” ሲሉ አክለዋል።

የሃማስ ተዋጊዎች ወደ ጋዛ ከወሰዷቸው ምርኮኞች መካከል ሴቶች፣ህጻናት እና አዛውንቶች ይገኙበታል። ከሃማስ እና ከፍልስጤም ትክክለኛ ቁጥራቸው ግን ግልጽ አይደለም።

በሌላ መረጃ በእስራኤል የሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ ቢያንስ 260 ሰዎች ተገድለዳል።የእስራኤል የነፍስ አድን ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በሱፐርኖቫ የሙዚቃ ፌስቲቫል የሞቱት ሰዎች ቁጥር 260 መድረሱን የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን የሀገር ውስጥ አድን ኤጀንሲ ጠቅሰው ዘግበዋል።

በሙዚቃ ኮንሰርቱ 3 ሺ ያህል ሰዎች ተገኝተዋል።ዝግጅቱ የተካሄደው በኔጌቭ በረሃ፣ ኪቡዝ ሪም አቅራቢያ ሲሆን ከጋዛ ሰርጥ ብዙም ሳይርቅ ነበር።

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *