መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 29፤2016 – በእስራኤል ውስጥ 1,500 የሚሆኑ የሃማስ ተዋጊዎች አስከሬን ተገኘ

የእስራኤል ጦር በእስራኤል እና በጋዛ ሰርጥ አካባቢ ወደ 1,500 የሚጠጉ የሃማስ ተዋጊዎች አስከሬን ማግኘቱን ገልጿል። የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ሪቻርድ ሄክት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የጸጥታ ሃይሎች የጋዛ ሰርጥ ድንበርን ተቆጣጥረዋል ብለዋል። ከትናንት ማታ ጀምሮ ማንም እንዳልገባ እናውቃለን ነገር ግን ሰርጎ መግባት አሁንም ሊከሰት ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።

እስራኤል ቢያንስ 2.3 ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩባት የጋዛ ሰርጥ የየብስ፣ የአየር እና የባህር መስመር ላይ   “ጠቅላላ እገዳ” አውጃለች። የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት በተከበበው ቀጠና ለነዋሪዎች ምግብ፣ ውሃ ወይም ነዳጅ አይኖርም ብለዋል። በእስራኤል ጦር የሚፈፀመው እንዲህ ዓይነት የጋዛ ከበባ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሕግ መሠረት የጦር ወንጀል ነው።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሀገሪቱ ከሃማስ ጋር እያደረገች ያለውን ጦርነት ተከትሎ የመካከለኛው ምስራቅን የኃይል አሰላለፍ ለመለወጥ ቃል ገብተዋል። የ73 አመቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ለደቡብ እስራኤል ባለስልጣናት እንደተናገሩት “ሀማስ የሚያጋጥመው ነገር ከባድ እና አስከፊ ነው እንዲሁን የመካከለኛው ምስራቅን የኃይል አሰላለፍን እንለውጣለን” ብለዋል። “ይህ ጅምር ብቻ ነው ሁላችንም ከእናንተ ጋር ነን እናም በከፍተኛ ኃይል እናሸንፋቸዋለን።

የእስራኤል ጦር በአንድ ሌሊት በጋዛ ሰርጥ ከ200 በላይ ቦታዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።በጋዛ ሰርጥ የሚገኘውን የሪማል ሰፈር እና ካን ዮኒስ ከተማን ጨምሮ ከፍተኛ ድብደባን ጦሩ ፈፅሟል። ወታደሮቹ እንደተናገሩት የሃማስ ላ የሚሳኤል ሃይል ማጠራቀሚያ አፓርትመንት የጥቃት ኢላማ ነበር ተብሏል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *