መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 30፤2016 –በኢትዮጵያ 8 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች በጡት ካንሰር ይጠቃሉ ተባለ

በዓለም ላይ በዓመት 2.2 ሚሊዮን  የሚሆኑ ሴቶች በጡት ካንሰር እንደሚያዙ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በኢትዮጵያ አሁን ባለው  ወቅታዊ ሁኔታ  የጡት ካንሰር ከሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ማለትም ከካንሰር ህመሞች  በአንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።በዚህም በኢትዮጵያ በርካታ  ሴቶች በጡት ካንሰር እየተጠቁ መሆኑን እና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ እንደሚገኝ በአዳማ ከተማ  አጠቃላይ ሆስፒታል ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ቢኒያም ተፈራ  በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በጡት ካንሰር ተጠቂ የሚሆኑ ሴቶች በአብዛኛው ከ50 ዓመት በታች የሆኑ ሴቶች  መሆናቸው ተጠቁሟል። ከ70 እስከ 80 በመቶ የሚሆኑ ታማሚዎች  ወደ ሆስፒታል  የሚመጡት የህመሙ ደረጃ  አሳሰቢ ሁኔታ  ላይ ከደረሰ በኃላ መሆኑም ይበልጥ ህመሙን አስጊ አድርጎታል።

ማንኛውም ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ቢያንስ አንድ ጊዜ  ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ተጠቁሟል ።  እድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች በተመሳሳይ  በዓመት አንድ ጊዜ ህክምና ማድረግ እንዳለባቸው ተጠቁሟል ።

በኢትዮጽያ አሁን ባለው  ሁኔታ 8 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች በጡት ካንሰር እንደሚጠቁም  እና ህመሙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ቢኒያም ተፈራ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል።

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *