መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 30፤2016 –የጋዛ ብቸኛው የኤሌትሪክ ምንጭ በ12 ሰዓታት ውስጥ ኃይል መስጠት እንደሚያቆም ተነገረ

የፍልስጥኤም ኢነርጂ ባለስልጣን ሃላፊ ታፈር መሄም በአሁኑ ጊዜ ብቸኛው የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ከ 10 እስከ 12 ሰአታት ውስጥ ነዳጅ ጨርሶ ይጠፋል ሲሉ ተናግረዋል።

እስራኤል “ሙሉ በሙሉ ከበባ” በማወጇ ሰኞ ለጋዛ የምትሰጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቋርጣለች። የምግብ፣ የነዳጅ እና የውሃ አቅርቦትም እንደሚቋረጥ እስራኤል መዛቷ ይታወሳል። ጋዛ በሀማስ የምትመራ ሲሆን እስራኤል ደግሞ ማን እና ምን እቃዎች ድንበሯን መሻገር እንደሚችል ገድባለች።

በጋዛ ውስጥ 80 በመቶ ያህሉ ነዋሪዎች በሰብአዊ ርዳታ ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን ጦርነተ ከመጀመሩ በፊት የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ። እሮብ እለት የተባበሩት መንግስታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ ከቅዳሜ ጀምሮ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የምግብ ራሽን ማግኘት አልቻሉም ሲል አስታውቆ ነበር።

የእስራኤል አየር ሃይል በጋዛ ሰርጥ የለያቻውን የሀማስ ኢላማዎችን ለማጥቃት የጦር አውሮፕላኖችን እየተጠቀመ ይገኛን። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 450 ኢላማዎችን መምታቱን አስታውቋቃ። ወታደሮቹ መሬት ላይ የተመሰረቱ የሮኬት ማስወንጨፊያዎችንም እየተጠቀሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የጦሩ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ ከ 2006 ግጭት በኋላ በጋዛ ላይ እንዲህ አይነት ማስወንጨፊያ ሲጠቀሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ብለዋል።ሃማስ ከጋዛ የከፈተውን አስከፊ ጥቃት ከደረሰ ከአራት ቀናት በኋላ የእስራኤል የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አሁንም ከሲዴሮት ከተማ አስክሬን እያነሱ ይገኛል። በእስራኤል የሟቾች ቁጥር ከ1,200 የበለጠ ሲሆን ከ2,700 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *