መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 30፤2016 – ጦርነት ካልተጠናቀቀ በያዝናቸው ታጋቾች አንደራደርም ሲል ሀማስ አስታወቀ

የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ ኃላፊ ኢስማኢል ሃኒዬህ ጦርነቱ እስካልተጠናቀቀ ድረስ ከእስራኤል ጋር በያዝናቸው ታጋቾች አንደራደርም ሲሉ ተናግረዋል። “የተያዙትን የጠላት ታጋቾችን በተመለከተ ያነጋገሩን ወገኖች ይህ ፋይል ጦርነቱ ከማብቃቱ በፊት እንደማይከፈት አሳውቀናል” ብለዋል።  እስራኤል ሃማስ ቅዳሜ እለት ከደቡብ እስራኤል በከፈተው ጥቃት ከ100 እስከ 150 የሚደርሱ ሰዎችን አግቶ እንደያዘ ገምታለች።

በሌላ በኩል የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠ/ሚ አንቶኒዮ ታጃኒ ሃማስ በደቡብ እስራኤል ላይ ካደረሰው ጥቃት በኋላ የጣሊያን እና የእስራኤል ዜግነት ያላቸው ባልና ሚስት ጠፍተዋል ሲል ይፋ አድርጓል ። ምንም እንኳን አሁንም እርግጠኛ አለመሆን እንዳለ አጽንኦት ሰጥተው ቢናገሩም ትናንት ማምሻውን ለሬይ ቲቪ እንደተናገሩት “ታግተው ሊሆን ይችላል” ሲሉ አክለዋል።

ጥንዶቹ ሀማስ ቅዳሜ እለት ተኩሶ ከፍቶ በርካቶችን ከገደለ እና ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ሰዎችን አግቶ ከወሰደበት ስፍራ ታግቶ ከ100 በላይ አስከሬኖች በተገኙበት ኪቡትዝ ቤኢሪ ውስጥ ይኖሩ ነበር። የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጥንዶቹ ከቤተሰባቸው ለቀረበላቸው ጥሪ ምላሽ እንዳልሰጡ ገልፀው ጣሊያን ችግሩን ለመፍታት ከእስራኤል ጋር እየሰራች ነው ብሏል። “በአስተማማኝ ሁኔታ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተስፋ እናደርጋለን፣ አሁን ግን ምንም ተጨማሪ መረጃ” የለንም ሲሉ ታጃኒ ገልፀዋል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *