
እስራኤል በጋዛ እና ሊባኖስ ላይ ነጭ ፎስፈስ ኬሚካል መጠቀሟን ሂዩማን ራይትስ ዋች ገልጿል።
ተቋሙ ከሊባኖስ እና ጋዛ ባገኘዉ ተንቀሳቃሽ ምስዕል ተመልክቶ ማክሰኞ እና እና ረቡዕ እለት እስራኤል በሊባኖስ ድንበር ላይ በሚገኙ ሁለት ገጠራማ አካባቢዎች ላይ ነጭ ፎስፈረስ መጠቀሟን የሚያሳዩ መረጃዎችን አግኝቻለሁ ብሏል።
ኬሚካሉ ከፍተኛ የሆነ የእሳት ቃጠሎ እና ለህይወት ዘመን ስቃይ የሚጋልጥ መሆኑን በሂዩማን ራይትስ ዋች የመካከለኛው ምስራቅ እና የሰሜን አፍሪካ ዳይሬክተሩ ላማ ፋቂህ ተናግረዋል። ነጭ ፎስፈረስ መኖሪያ ቤቶችን በእሳት ሊታወድም እና በሰዎች ላይም ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ነዉ ተብሏል።
ተቋሙ እስራኤል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የኬሚካል ጦር መሳሪያ መጠቀሟን እንድታቆም ጠይቋል።
ሃማስ ባሳለፍነው ቅዳሜ በእስራኤል ላይ ያለተጠበቀ እና ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘረሩን ተከትሎ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የተጀመረው ጦርነት ዛሬ ሰባተኛ ቀኑን ይዟል።በሃማስ ጥቃት እና በእስራኤል የአየር ድብደባ ከሁለቱም ወገኖች የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሺህ 800 ማለፉ ተነግሯል።
እስራኤል ባወጣችው መረጃ መሰረት በሃማስ ጥቃት የሞቱ እስራኤላውያን ቁጥር 1300 የደረሰ ሲሆን፤ ከ3 ሸህ 300 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
በስምኦን ደረጄ