መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 2፤2016 –በኢትዮጵያ አንዲት እናት በአማካይ ከ 4 በላይ ልጆችን ትወልዳለች ተባለ

???????? በአዲስአበባ ያለዉ የዉልደት ምጣኔ ጤናማ ደረጃ ላይ ሲገኝ ለዚህ የኑሮ ዉድነቱ አስተዋጽኦ አድርጓል ተብሏል

በኢትዮጵያ የቤተሰብ እቅድ አጠቃቀም በየጊዜዉ መሻሻል እያሳየ ቢሆንም አሁንም ግን ከፍተኛ የዉልደት ምጣኔ ካላቸዉ ሀገራት ተርታ ዉስጥ ከመቀመጥ አልገታትም።

በአፍሪካ ሁለተኛዉ የህዝብ ቁጥር ብዛት ባለቤት በሆነችዉ ኢትዮጵያ የምትገኝ አንዲት ሴት አልያም እናት በአማካይ 4.1 ልጆችን እንደምትወልድ በጤና ሚኒስቴ የእናቶች ህጻናትና አፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎት የስነ-ተዋልዶ ፣ ቤተሰብ እቅድና የጤና ዴስክ ሀላፊ ዶ/ር አለማየሁ ሁንዱማ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

“የቤተሰብ እቅድ መጠቀም የህዝብ ቁጥርን መቀነስ አይደለም” ያሉት ዶ/ር አለማየሁ አላማዉ ወላጆች ልጆቻቸዉን ካላቸዉ ኢኮኖሚያዊ አቅም እና ጤናማ የልጆች ዉልደትን በተከተለ መልኩ እንዲተገብሩ ማድረግ ነዉ ብለዋል።

የአንድ ሀገር አማካይ ጤናማ የዉልደት ምጣኔ 2.1 መሆን እንዳለበት ቢመከርም በኢትዮጵያ ያለዉ ወቅታዊ ምጣኔ ግን የዚህ እጥፍ እድገት አስመዝግቦ ተቀምጧል።

ከ 120 ሚሊዮን በላይ ዜጎች እንደሚኖሩባት የምትገመተዉ ኢትዮጵያ የዉልደት ምጣኔዋ አሁን መቀነስ አሳይቷል ተብሏል። በየ አምስት አመቱ የዉልደት ምጣኔ የሚገኝበት ደረጃ እንደሚጠና የነገሩን ዶ/ር አለማየሁ ፤ ምጣኔዉ ከዚህ ቀደም 4.6 በመቶኛ እንደነበር ገልጸዋል።

አዲስአበባ ከተማ ከሌሎች አካባቢዎች ጤናማ የሆነዉ የዉልደት ምጣኔ ያለባት ከተማ ስትሆን ይህም 2.1 በመቶ መሆኑን ዶ/ር አለማየሁ ገልጸዋል። ለዚህም ደግሞ የኑሮ ዉድነቱ አንዱ የቤተሰብ ምጣኔን ለማስተካከል አስተዋጽኦ እንዳለዉ ጨምረዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በአለማችን ኒጀር ፣ ቻድ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቀደሚ ከፍተኛ የዉልደት ምጣኔ ያለባቸዉ ሀገራት ናቸዉ።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *