
አንድ ታዋቂ ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ በቴሌቭዥን ቃለ ምልልስ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒን በመሳደብ የስም ማጥፋት ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ሮቤርቶ ሳቪያኖ ጠ/ሚ ሜሎኒ በታህሳስ 2020 በስደት ላይ ያላትን አቋም ተከትሎ የስድብ ቃል ተጠቅመዋል።
የ 1,000 ዩሮ ቅጣት የሚከፍለው ምንም እንኳን ጥፋቱን ከደገመ በኃላ ቢሆንም የመብት ተሟጋቾች ግን የፕሬስ ነፃነት የሚጋፋ ነው ብለዋል። ሳቪያኖ ከፍርድ ቤቱ በራፍ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የሜሎኒ መንግስት በስደተኞች ላይ “ማስፈራራት” አድርሷል ሲል አስታውቋል።
ሜሎኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት በታህሳስ 2020 በተደረገ የቴሌቪዥን ቃለ መጠይቅ ላይ ስደተኞችን የጫኑ ጀልባዎች መስጠም አለባቸው ማለታቸውን ተከትሎ ነው። የፔን ኢንተርናሽናል ደራስያን ማኅበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክሱን እንዲያቋርጡ አሳስቦ የነበረ ቢሆንም፣ ወይዘሮ ሜሎኒ ግን ምንም ምክንያት እንዳላዩ ገልፀዋል።፣ ውሳኔው የዳኞች እንደሆነ ተነግሯል።
በኤደን ሽመልስ