መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 2፤2016 –????????????????አጫጭር መረጃዎች በእስራኤል ሃማስ ጦርነት ዙሪያ

????????????????የእስራኤል ጦር በጋዛ ላይ በራሪ ወረቀት በመበተን ነዋሪዎች አካባቢያቸውን እንዲለቁ አስጠንቅቋል።የእስራኤል ጦር ነዋሪዎች ወደ ደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል እንዲሸሹ የሚያስጠነቅቅ በራሪ ወረቀቶችን በጋዛ ላይ ጥሏል።

????????????????”ቤቶቻችሁን አሁኑ ለቃችሁ ከዋዲ ጋዛ ወደ ደቡብ ውጡ” የሚል በራሪ ወረቀቶች ከድሮኖች ላይ ተለቀዋል። በራሪ ወረቀቶች ላይ በሰፈረው ካርታ መሰረት ከማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ ወደ ደቡብ የሚያመለክት ቀስት አሳይቷል።

????????????????ሃማስ ቅዳሜ እለት ጥቃት ካደረሰ ወዲህ 6,000 ቦምቦችን በጋዛ ሰርጥ ላይ እስራኤል መወርውራለች። ይህም ዩናይትድ ስቴትስ በአፍጋኒስታን ለአንድ ዓመት ከተጠቀመችበት የቦምብ ብዛት ጋር እኩል ሲሆን እስራኤል በሰባት ቀናት ውስጥ ተጠቅማዋለች። አፍጋኒስታን ከጋዛ ሰርጥ 1,800 እጥፍ ጊዜ ትበልጣለች።

???????????????????????? የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቤጂንግ በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ሰራተኛ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል። ከማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተወሰደ ነው ምስል እንዳመላከተው አንድ ሰው በመንገድ ላይ በቢላ ሲጠቃ ያሳያል። አርብ የተፈጸመው ጥቃት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ያልተፈፀመ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ እየተጣራ መሆኑን የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። መግለጫው “ሰራተኛው በሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት እና በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ነው” ይላል.።

????????????????????????በቻይና ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከቅርብ ቀናት ወዲህ ለፍልስጤማውያን ሰፊ ድጋፍ ያሳዩ ሲሆን በድረ-ገጽ ላይ ፀረ እስራኤል ፅሁፎችም ታይተዋል። አንዳንዶች እስራኤል ከታይዋን ጋር ባላት ግንኙነት ተችተዋል። ቻይና ስለ እስራኤል-ሐማስ ጦርነት “በጣም እንዳሳሰባት” እና “በግጭቱ ምክንያት በሲቪል ዜጎች ላይ በደረሰው ጉዳት አዝኛለሁ” ስትል ተናግራለች። በምላሹ እስራኤል በቻይና የሃማስ ጥቃት ላይ ውግዘት ባለማግኘቷ “የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን” ገልጻለች።

????????????????የእስራኤል ሰሜናዊ ድንበር ውጥረት ባለበት በአሁኑ ወቅት የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዶላሂን ጎረቤታቸውን ሊባኖስን የጎበኙ ሲሆን ከሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ ጋር ተገናኝተዋል።

????????????????በጋዛ ፍልስጤማውያን ላይ የሚፈፀመው የጦር ወንጀሎች ያለ ጥርጥር የጋራ ምላሽ እንደሚፈጥር አስጠንቋቀዋል። ሄዝቦላህ ፍልስጤማውያን አጋሮችን በመደገፍ እስራኤልን ለማጥቃት ከወሰነ በጦርነቱ ውስጥ አዲስ ግንባር ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት አይሏል።  የሂዝቦላህ ምክትል መሪ ከእስራኤል ጋር በሚደረገው ጦርነት ከሃማስ ጋር ለመቀላቀል ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

????????????????በቤይሩት በተካሄደው ሰልፍ ላይ የተናገሩት ኃላፊው “ጊዜው ሲደርስ” ጣልቃ እንደሚገቡ ገልፀዋል። ልክ እንደ ሀማስ፣ ሂዝቦላህ በእንግሊዝ፣ በአሜሪካ እና በሌሎች ሀገራት የሽብር ድርጅት ተብሎ ተፈርጇል። በሊባኖስ ውስጥ በወታደራዊ እና በፖለቲካዊ መልኩ ከፍተኛ ሚና ያለው ቡድኑ ለኢራን ቅርብ ነው።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *