????በዛሬው እለት ዓለም አቀፉ የአንስቴዥያ ባለሙያዎች ቀን እየተከበረ ይገኛል
በመጀመሪያ ዲግሪ እና በማስተርስ ደረጃ የተመረቁ 3ሺ የሚሆኑ አኒስቴዥያ ባለሙያዎች መኖራቸውን የኢትዮጵያ አኒስቴቲስቶች ማህበር አስታውቋል።የማህበሩ ዋና ጸሀፊ እና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአኒስቴዥያ ክፍል ኃላፊ ዶክተር አናንያ አባተ ከብስራት ሬድዮና ቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት የዓለም ጤና ድርጅት 4 በዶክተር ደረጃ ያሉት አኒስቴዥያ ባለሙያዎች ለመቶ ሺ ብሎ ቢያስቀምጥም በኢትዮጵያ ለ120 ሚሊየን ሰዎች 200 ብቻ በዶክተር ደረጃ የሚገኙ አኒስቴዥያ ባለሙያዎች አገልግሎት እየሰጡ ነው ብለዋል።
እንደሀገር ይህንን ችግር ለመቅረፍ የአንስቴዥያ ባለሙያዎች እንደ የትምህርት ደረጃቸው ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ተብለው አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ ይገኛል።በአጠቃላይ በኢትዮጲያ ያለው የአኒስቴዥያ ባለሙያዎች ቁጥር ከ3ሺ በመካከለኛ እና ዝቅተኛ እንዲሁም ሁለት መቶ በከፍተኛ ባለሙያ ሆነው ከአንድ መቶ ሀያ ሚሊየን በላይ ህዝብ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል።
በአንድ ዩንቨርስቲ ውስጥ ብቻ ይሰጥ የነበረውን ከፍተኛ አኔስቴዥያ ባለሙያዎች ትምህርት በስምንት ዩንቨርስቲዎች እንዲሰጥ በማድግ ማስተማር መጀመሩን ዶክተር አናንያ አንስተዋል።
የአኔስቴዥያ ባለሙያዎች ቁጥር ማነስ በኢትዮጵያ የሚሰጡ የቀዶ ህክምና አገልግሎቶች ሪፈር እንዲበዛባቸው እና በማደንዘዣ የሚሰጡ ምርመራዎች ላይ ክፍተት መፍጠሩን ዶ/ር አናንያ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
በህክምና ወቅት አኔስቴዥያ የሚያስፈልገው ታካሚን የጤና ሁኔታ በዝርዝር አለማወቅ እና ከፍተኛ ደረጃ ያሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ማነስ በህክምና ላይ እክል እንዲገጥም ከማረጉም ባሻገር ህይወት ሊያሳጣ እንደሚችል ተጠቁማል፡፡
በዛሬው እለት በአለም አቀፍ ደረጃ የአኒስቴዥያ ቀን አንስቴዥያ እና የካንሰር ህክምና በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።
በትግስት ላቀው